ቤታኒ በኢትዮጵያ

አፍቃሪ ቤተሰብ፤ ለእያንዳንዱ ወንድ፣ ሴት ልጅ እና ታዳጊ።

ቤታኒ በኢትዮጵያ

አፍቃሪ ቤተሰብ፤ ለእያንዳንዱ ወንድ፣ ሴት ልጅ እና ታዳጊ።

ለችግር የተጋለጡ ልጆችን እና ቤተሰቦችን እንረዳለን።

ኢትዮጵያ ከ5 ሚሊዮን በላይ ወላጅ አልባ ሕፃናት አሏት። ቢታኒ ኢትዮጵያ ለእያንዳንዱ ልጅ አፍቃሪ ቤተሰብ ይገባዋል ብሎ ያምናል። ለዛ ነው ለአደጋ የተጋለጡ ቤተሰቦችን ለልጆቻቸው አስተማማኝ እና አፍቃሪ ቤት ማቅረባቸውን እንዲቀጥሉ ለመደገፍ፣ ለማጠናከር እና ለማበረታታት የምንሰራው። በጉዲፈቻ ማደጎ፣ ወላጅ አልባ ለሆኑ ህጻናት ቋሚ አማራጭ የቤተሰብ እንክብካቤ እንሰጣለን። በተጨማሪም በጋምቤላ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች ለደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች የስነ ልቦና ድጋፍ እንሰጣለን እንዲሁም ወዳጅ ለሌላቸው ወይም ከወላጆቻቸው ለተለያዩ ህጻናት ቤተሰብን መሰረት ያደረገ እንክብካቤ እናደርጋለን።

የቤተሰብ እንክብካቤ እና ማበረታታት

ማደጎ/ ጉዲፈቻ

የቢታኒን ስራ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመደገፍ ይለግሱ

በኢትዮጵያ ቀዳሚ ተግባራችን ልጆች ከትውልድ ቤተሰባቸው ጋር ተረጋግተው ደህንነታቸውም ተጠብቆ እንዲኖሩ ነው። ይህ በማይሆንበት ጊዜ፣ በአቅራቢያቸው ያሉ ማደጎ ሚወስዱ አፍቃሪ ቤተሰቦችን ፈልገን እናገኛለን።

የእርስዎ ስጦታ ቤተሰቦችን አንድ ላይ ለማቆየት ይረዳል።